hatauu

hatauu

86p

51 comments posted · 16 followers · following 0

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ‹‹በኢ... · 0 replies · +2 points

ይህ መንግስት ልማት ልማት ብቻ አይሁን መዝሙሩ! ልማትና ዴሞከራሲ አይነጣጠሉም፡፡ ሁለቱንም ጎን ለጎን እኩል ቢያሰኬዳቸው እወዳለሁ፡፡ እኔ የሚገርመኝ ዛሬም ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግና ድምጻቸውን ለማሰማት ሰፈልጉና ሲከለከሉ አዝናለሁ፡፡ ይህ መንገስት/ በተለይ ኢህአዴግ አሁንም በሩን ጠርቅሞ የመዝጋት አባዜ ውስጥ እንዳለ ነው የሚያሳየው፡፡ ይህ ጥሩ አይደለም! የበለጠ ሊቆጣጠረው የማይችለው ችግር ፈንድቶ ሀገሪቱን እንዳየጎዳ እሰጋለሁ፡፡

ለማንኛውም መንግስትን ለሚመሩትም ሆነ ተቃዋሚ መሪዎችና ዜጎች ማስተዋሉን ጌታ እንዲሰጣቸው እፀልያለሁ! ሁሉም ኢትዮጵያን እንዲጠቅሙ ጌታ ይባርክ! አሜን!!!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የግብፅ የጦር... · 0 replies · +10 points

አቦ አታስፈራሩን! -ጦርነትን እንደሆነ እናውቀዋለን ከአሁን በኋላ በረሀብ ከማለቅ በጦርነት እንደሚሻል ተረድተናል፡፡ ለዚህም ሲባል አባይን ገድበን ሀገራችንን ለማልማት ከረሀብ ለመውጣት ቆርጠናል፡፡ እንግዲህ አትገድቡም ካለችሁ የጦርነት መንገድ ከመረጣችሁ ምንገዶን እኛ? ይዋጣልና!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - በዓረና ትግራ... · 0 replies · +2 points

You doubt everything? I have been doubting things a lot. We could experience doubt on things going at one or another time. That's normal . But I never doubt that the government can't do it as long as it thinks it will gain out of it. The very nature of the EPRDF and its old fashioned of weakening its opponents (opposition parties) will certainly make you believe what has been done on Arena.

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - በዓረና ትግራ... · 0 replies · +1 points

@ kalayu

I wish I would speak Tigrigna. I am sorry I can't understand what you are saying as you are not writing in the language most people will understand. what if you write in Amharic or English and let have a good debate here. You may not be wanting to communicate with people coming to this debate board. If that is your goal, why do you need to say it in Tigrigna?

I wish you come again and have you say it in Amharic or English. Then we will communicate. Bye till then.
God Bless You!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - በዓረና ትግራ... · 2 replies · +16 points

አስቂኝ ነገር ነው እንደው:: ግን እንደህ አይነት ድራማ የሚሰራው ይህ መንግስት ከሆነ ማፍር አለበት! በጣም አስቂኝና አሳፋሪ ነው እኮ ጎበዝ!
በአቅምቲ ብዙ መጽሀፍ እንብቤያለሁ ብዬ አስባለሁ:: ይሁንና እንዲህ አይነት ድራማ የሚጫወቱ መንግስታት መኖራቸውን አላነበብኩም ከአፍሪካ ሀገራት እንኳን! በጣም አሳፋሪ አሳፋሪ! አስገራሚው ደግሞ አሁንም በዶክተር መረራ ነባሩ ኦብኮ ላይ የተፈጸመው አይነት ድርጊት ነው በተመሳሳይ መልኩ ዓረና ላይ የተፈጸመው:: ግን ይህ ጥሩ ነው? የምናየው ይሆናል::

እ/ር ልቦናውን ይስጣችሁ ብቻ!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የአፍሪካ ኅብ... · 0 replies · +14 points

የሚገርመው የዜናው ርዕስ በዜናው ውስጥ ካለው ታሪክ ጋር ተመጣጣኝ ሆኖ አላገኘሁትም:: ምንድን ነው ሪፖርተር ሊነግረን የፈለገው? አልገባኝም! ምንድን ነው የመሪዎቹ ስብስባ ፋይዳ? አልተገለጻም:: በእርግጥ የአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባዎች የሚወራለትን ያህል በጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔ የሚያሳልፍ አይደለም:: መሪዎቹ ብዙውን ጊዜ ለሽርሽር የሚመመጡ ወይም የሚሰበሰቡ ይመስላሉ:: እንደ እውሮፓ ህብረት እና ተመድ ስብስባዎች የረባ ፋይዳ የሚገኝበት አይደለም:: ሌላው ብዙ የአፍሪካ ሀገር መሪዎች ክስን ይፈሩታል:: በአለም አቀፍ ተቋማት የሚወጡባቸውን የክስ ዋራንቶች ህብረቱን በማስተባበር በጋራ አቋም ሲይዙ ይታያል:: አሁንም የሆነው ይህ ነው መሰረታዊ በሚባሉ የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ሳየነጋገር በቸልታ ማለፍ ምን ይሉታል-አጀንዳ አልተያዘም ብሎ ነገር? ሙሴቬኒ ጥርጣሬ ገብቷቸው የኮትዲቯር ምርጫ ይጣራ አሉ:: ሀሪፍ ቀልድ ነው! ዣፒንግና የኬንያ ባለስላጣናትም ተመሳሳይ አቋም ያዙ:: ሀሪፍ ቀልድ አይደል!

መሰታወት ቤት ውስጥ ያለ ድንጋይ አየወረውርም ነው ነገሩ! ምንድን ነው ፋይዳው እንግዲህ? ሆያ ሆዬ ብቻ ነው ስብሰባው! በሀገራት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም የሚል አህጉራዊ ድርጅት? ቀልድ ነው! ሪፎርም ያስፈልገዋል ህብረቱ ራሱ ገና!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የህንዱ ኩባን... · 1 reply · +1 points

@hibir

are you referring to me or justinbk? I am unclear, sorry!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - መንግሥት ያስ... · 1 reply · +4 points

አሁን ምን እንዳሳሰበኝ ታውቃላችሁ? ግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ! ብዙ ሀገሮች ዜጎቻቸውን እያስወጡ ነው:: የእኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ምን እየሰራ ይሆን? እባካችሁ ሪፖርተሮች ፈጥናችሁ ይህን ጉዳይ አሳውቁን:: ብዙ ኢትዮጵያውያን ግብጽ እንደሚኖሩ አውቃለሁ- በተለይ ሴት እሀቶቻችን::

እ/ር ከክፉ ሁሉ እንዲጠብቃቸው እንፀልይ!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - ጓደኛዋን የዘ... · 0 replies · 0 points

JESUS!

13 years ago @ Reporter - Amharic Ver... - የህንዱ ኩባን... · 8 replies · +5 points

ይህ ዜና ርዕስ በጣም የጮሀ ይመስለኛል:: የአዲስ አበባ ሁለት እጥፍ መሬት ለምን ፈለገ? ይህ ትልቅ ጥናት የሚፈልግና ተንትኖ ማየት የሚጠይቅ ይመስለኛል:: ምናልባት ጋዜጠኞችንም ይበልጥ ምርምርና ጥናት እንዲያደርጉ የሚጋብዝ ነገር ነው:; የአዲስ አበባን ሁለት እጥፍ መሬት የፈለገ ኩባንያ ነገ ሁለትና ሶስት ክልሎችን ለመቀራመት የማይንደረደርበት ምክንያት አይታየኝም:: ገና ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ (በ1995) ወደ አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስሄድ የሰማሁትን ታሪክ ያስታውሰኛል ጅቡቲ ከኢትዮጵያ እንዴት እንደሄደች አፋሮች የነገሩኝን ታሪክ!

መንግስት ገና ለገና መሬት ያለማሉ በሚል መሬት በውጭ ባለሀብት እንዲያዝ የሚፈቅድ ከሆነ አደጋው የከፋና የሰፋ ነው የሚሆነው:: በተለይም በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉትን መሬቶች በልማት ሰበብ/አማካኝነት አሳልፎ ለውጭ ዜጎች የሚሰጥ ከሆነ ራሱ ላይ የሚነድ ቤንዚን እየፈበረከ/እያዘጋጀ እንደሆነ ልብ ይበል! ሌላው ቢቀር ባለሀብት ተብዬዎቹ ምናለ ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ! ቆም ብሎ እየተስተዋለ! አደጋው ብዙ ነው:: ትንቢት እንዳይሆንብኝ!